11 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤“በእርግጥ ለበጎ ዐላማ እታደግሃለሁ፤በመከራና በጭንቅ ጊዜም፣ጠላቶችህ ደጅ እንዲጠኑህ በእውነት አደርጋለሁ።
12 “ሰው ብረትን፣ ከሰሜን የመጣን ብረት፣ነሐስንስ መስበር ይችላልን?
13 በመላ አገርህ፣ስላለው ኀጢአትህ ሁሉ፣ሀብትና ንብረትህን፣ያለ ዋጋ አሳልፌ ለምርኮ እሰጣለሁ።
14 ቍጣዬ በላያችሁ፣የሚነድ እሳት ትጭራለችና፣በማታውቀው አገር፣ለጠላቶችህ ባሪያ አደርግሃለሁ።”
15 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ፤እንግዲህ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ።ታጋሽ እንደ መሆንህ አታጥፋኝ፤ባንተ ምክንያት የሚደርስብኝን ነቀፋ አስብ።
16 ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በስምህ ተጠርቻለሁና፣ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።
17 ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋር አልተቀመጥሁም፤ከእነርሱም ጋር አልፈነጨሁም፤እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣ለብቻዬ ተቀመጥሁ።