ኤርምያስ 38:19-25 NASV

19 ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን፣ “ወደ ባቢሎን የኰበለሉት አይሁድ እንዲያላግጡብኝ፣ ባቢሎናውያን ለእነርሱ ዐሳልፈው ይሰጡኛል ብዬ እፈራለሁ” አለው።

20 ኤርምያስም እንዲህ አለው፤ “ዐሳልፈው አይሰጡህም፣ ብቻ የምነግርህን የእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ፤ መልካም ይሆንልሃል፤ ሕይወትህም ትተርፋለች።

21 እጅህን ለመስጠት እንቢ ብትል ግን፣ እግዚአብሔር የገለጠልኝ ነገር ይህ ነው፤

22 በይሁዳ ቤተ መንግሥት የቀሩ ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ባለ ሥልጣኖች ይወሰዳሉ፤ ሴቶቹም እንዲህ ይላሉ፤“ ‘እነዚያ የተማመንህባቸው ወዳጆችህ፣አሳሳቱህ፤ አሸነፉህ።እግርህ ጭቃ ውስጥ ተሰንቅሮአል፣ወዳጆችህ ጥለውህ ሄደዋል።’

23 “ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ተወስደው ለባቢሎናውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ራስህ በባቢሎን ንጉሥ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”

24 ሴዴቅያስም ኤርምያስን እንዲህ አለው፤ “ስለዚህ ስለ ተነጋገርነው ነገር ማንም አይወቅ፤ አለዚያ ትሞታለህ።

25 መኳንንቱ ከአንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ ሰምተው ወደ አንተ ቢመጡና፣ ‘ንጉሡን ምን እንዳልኸው፣ ንጉሡም ምን እንዳለህ ንገረን፤ ሳትደብቅ ንገረን፤ አለዚያ እንገድልሃለን’ ቢሉህ፣