3 ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና፣ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።
4 ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ቀኑ ደርሶአልና። እግዚአብሔር በከፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋተነሥቶአል።
5 ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፣አስቀሎና አፏን ትይዛለች።በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ትሩፋን ሆይ፤እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ?
6 “ ‘የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ፤የማታርፈው እስከ መቼ ነው?ወደ ሰገባህ ተመልሰህ ግባ፤ጸጥ ብለህ ተቀመጥ’ ትላላችሁ።
7 ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣እንዲወጋ ሲያዝዘው፣እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣እንዴት ማረፍ ይችላል?”