ሕዝቅኤል 26:13-19 NASV

13 ዘፈንሽን ጸጥ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም የበገናሽ ድምፅ አይሰማም።

14 የተራቈተ ዐለት አደርግሻለሁ፤ የመረብ ማስጫ ቦታ ትሆኛለሽ፤ እንደ ገናም ተመልሰሽ አትሠሪም እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁና፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’

15 “ጌታ እግዚአብሔር ጢሮስን እንዲህ ይላል፤ ‘የቈሰሉት ሲያቃስቱ፣ በውስጥሽም ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሣ ደሴቶች አይነዋወጡምን?

16 የባሕር ጠረፍ መሳፍንት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ይጥላሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ። ፍርሀት ተከናንበው በመሬት ላይ በመቀመጥ ባለማቋረጥ፣ እየተንቀጠቀጡ በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ይሸበራሉ፤’

17 ስለ አንቺም እንዲህ ብለው ሙሾ ያወርዳሉ፤“በባሕር ሰዎች የሚኖሩብሽ፣ባለዝናዋ ከተማ ሆይ፤ እንዴት ጠፋሽ!ከነዋሪዎችሽ ጋር፣የባሕር ላይ ኀያል ነበርሽ፤በዚያ በሚኖሩትም ሁሉ ዘንድየተፈራሽ ነበርሽ።

18 አሁን በመውደቂያሽ ቀን፣በጠረፍ ያሉ አገሮች ተናወጡ፤ከመፍረስሽም የተነሣ፤በባሕር ውስጥ ያሉ ደሴቶች ተደናገጡ።”

19 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የውቅያኖስንም ውሃ በላይሽ አድርጌ በቀላይ ስሸፍንሽ፣