ሕዝቅኤል 27:7-13 NASV

7 የመርከቦችሽ ሸራ ጥልፍ ሥራ ያለበት የግብፅ በፍታ ነበረ፤ይህም እንደ ዐርማ አገለገለሽ።መጋረጃዎችሽ ከኤሊሳ ጠረፍ የመጡ፣ባለ ሰማያዊና ሐምራዊ ቀለም ነበሩ።

8 ቀዛፊዎችሽ ከሲዶናና ከአራድ የመጡ ነበሩ፤ጢሮስ ሆይ፤ የራስሽ ጠቢባን የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።

9 ልምድ ያካበቱ የጌባል ባለ ሙያዎች፣መርከብሽን ለመገጣጠም በመካከልሽ ነበሩ፤የባሕር መርከቦችና መርከበኞቻቸው ሁሉ፣ከአንቺ ጋር ሊገበያዩ ይመጡ ነበር።

10 “ ‘የፋርስ፣ የሉድና የፉጥ ሰዎች፣ወታደር ሆነው በሰራዊትሽ ውስጥአገለገሉ፤ሞገስም ይሆኑሽ ዘንድ፣ጋሻቸውንና የራስ ቍራቸውን በግድግዳሽ ላይ ሰቀሉ።

11 የአራድና የሔሌክ ሰዎች፣ቅጥርሽን በየአቅጣጫው ጠበቁ፤የገማድ ሰዎችም፣ በምሽግሽ ውስጥ ነበሩ።ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።

12 “ ‘ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ፣ ተርሴስ ከአንቺ ጋር የንግድ ልውውጥ ታደርግ ነበር፤ ብርና ብረት፣ ቈርቈሮና እርሳስ አምጥታ ሸቀጥሽን ትለውጥ ነበር።

13 “ ‘ያዋን፣ ቶቤልና ሞሳሕ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር፤ ባሪያዎችንና የናስ ዕቃዎችን በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።