ሕዝቅኤል
ምዕራፎች 30:18-24
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
18የግብፅን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል።በደመና ትሸፈናለች፤መንደሮቿም ይማረካሉ።
19ስለዚህ በግብፅ ላይ ቅጣቴን አመጣለሁ፤እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
20በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር በሰባተኛው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
21“የሰው ልጅ ሆይ፤ የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ ይፈወስ ዘንድ ክንዱ አልተጠገነም፤ ወይም ሰይፍ መያዝ ይችል ዘንድ እጁ በመቃ አልታሰረም።
22ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነሥቻለሁ፤ ደኅናውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ።
23ግብፃውያንን በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።
24የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል።