1 “አንተም፤ የሰው ልጅ ሆይ፤ የተሳለ ሰይፍ ወስደህ እንደ ጢም መላጫ ጠጒርህንና ጢምህን ተላጭበት፤ ጠጒሩንም በሚዛን ከፋፍል።
2 የከበባው ጊዜ ሲፈጸም የጠጒሩን ሢሶ በከተማው ውስጥ አቃጥለው፤ ሌላውን ሢሶ ጠጒር በከተማዪቱ ዙሪያ ሁሉ በሰይፍ ቈራርጠው፤ የቀረውንም ሢሶ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በተመዘዘ ሰይፍ አሳ ድዳቸዋለሁና።
3 ደግሞም ከጠጒሮቹ ጥቂት ወስደህ በመጐናጸፊያህ ጫፍ ቋጥር፤
4 እንደ ገናም ከእነዚህ ጥቂት ወስደህ እሳት ውስጥ ጨምራቸው፤ አቃጥላቸውም። እሳትም ከዚያ ወጥቶ ወደ እስራኤል ቤት ሁሉ ይሰራጫል።
5 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አገሮችን በዙሪያዋ ሁሉ አድርጌ፣ በአሕዛብም መካከል ያስቀመጥኋት ኢየሩሳሌም ይህች ናት።
6 እርስዋም በዙሪያዋ ካሉት አገሮችና አሕዛብ ይልቅ በሕጌና በሥርዐቴ ላይ በክፋቷ ዐመፀች፤ ሕጌን ጥላለች፤ ሥርዐቴንም አልተከተለችም።”