ሕዝቅኤል 5:3-9 NASV

3 ደግሞም ከጠጒሮቹ ጥቂት ወስደህ በመጐናጸፊያህ ጫፍ ቋጥር፤

4 እንደ ገናም ከእነዚህ ጥቂት ወስደህ እሳት ውስጥ ጨምራቸው፤ አቃጥላቸውም። እሳትም ከዚያ ወጥቶ ወደ እስራኤል ቤት ሁሉ ይሰራጫል።

5 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አገሮችን በዙሪያዋ ሁሉ አድርጌ፣ በአሕዛብም መካከል ያስቀመጥኋት ኢየሩሳሌም ይህች ናት።

6 እርስዋም በዙሪያዋ ካሉት አገሮችና አሕዛብ ይልቅ በሕጌና በሥርዐቴ ላይ በክፋቷ ዐመፀች፤ ሕጌን ጥላለች፤ ሥርዐቴንም አልተከተለችም።”

7 “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብ ይልቅ ሞገደኞች ሆናችኋል፤ ሥርዐቴን አልተከተላችሁም፤ ለሕጌም አልታዘዛችሁም። በዙሪያችሁ የሚገኙ አሕዛብ የሚጠብቁትን ሕግ እንኳ አልጠበቃችሁም።

8 “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ፤ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ተነሥቻለሁ፤ በአሕዛብም ፊት ፍርድ አመጣብሻለሁ።

9 በጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ ምክንያት ካሁን ቀደም ያላደረግሁትን፣ ወደ ፊትም የማላደርገውን በአንቺ ላይ አደርጋለሁ።