17 ፍትሕን የመለኪያ ገመድ፣ጽድቅንም ቱንቢ አደርጋለሁ፤ውሸት መጠጊያችሁን የበረዶ ዝናብ ይጠራርገዋልመደበቂያችሁንም ውሃ ያጥለቀልቀዋል።
18 ከሞት ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳን ይሻራል፤ከሲኦልም ጋር ያደረጋችሁት ስምምነት ይፈርሳል፤ታላቁ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣እናንተም ትጠራረጋላችሁ።
19 በመጣ ቍጥር ይዞአችሁ ይሄዳል፤ማለዳ ማለዳ፣ በቀንና በሌሊትምይጠራርጋል።”ይህን ቃል ብታስተውሉ፣ሽብር በሽብር በሆነ ነበር።
20 እግር ዘርግቶ እንዳይተኛ ዐልጋው አጭር ነው፤ሰውነትንም ለመሸፋፈን ብርድ ልብሱ ጠባብ ነው።
21 እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።
22 እንግዲህ ፌዛችሁን አቁሙ፤አለዚያ እስራታችሁ ይጸናባችኋል፤ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣መላውን ምድር ለማጥፋት ያወጀውን ዐዋጅ ሰምቻለሁ።
23 አድምጡ ድምፄን ስሙ፤አስተውሉ ቃሌንም ስሙ።