1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እናታችሁን የፈታሁበትየፍቺ ወረቀት የት አለ?ወይስ እናንተን የሸጥኋችሁለየትኛው አበዳሪዬ ነው?እነሆ፤ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ስለ መተላለፋችሁም እናታችሁ ተፈታለች።
2 በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም?በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ?ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ አጥራ ነበርን?እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን?እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤በጥማትም ይሞታሉ።
3 ሰማይን ጨለማ አለብሰዋለሁ፤ማቅን መሸፈኛው አደርጋለሁ።
4 ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤በየማለዳው ያነቃኛል፤በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።
5 ልዑል እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶታል፤እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም።
6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢሜን ለሚነጩ ጒንጬን ሰጠሁ፤ፊቴን ከውርደት፣ከጥፋትም አልሰወርሁም።
7 ልዑል እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልዋረድም፤ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይአድርጌአለሁ፤እንደማላፍርም ዐውቃለሁ።