ኢሳይያስ 54:4-10 NASV

4 “አይዞሽ አትፍሪ፤ ኀፍረት አይገጥምሽም፤ውርደት ስለማይደርስብሽ አትሸማቀቂ፤የወጣትነት ኀፍረትሽን ትረሺዋለሽ፤የመበለትነት ስድብሽንም ከእንግዲህ አታስታውሺውም።

5 ባልሽ ፈጣሪሽ ነውና፤ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ታዳጊሽ የእስራኤል ቅዱስ ነው፤እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።

6 እንደ ተናቀች የልጅነት ሚስት፣ከልብ እንዳዘነችና እንደ ተጠላች ሚስት፣ እግዚአብሔር እንደ ገና ይጠራሻል”ይላል አምላክሽ።

7 “ለጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፤ነገር ግን በታላቅ ርኅራኄ መልሼ እሰበስብሻለሁ።

8 ለጥቂት ጊዜ እጅግ ስለ ተቈጣሁ፣ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፤ነገር ግን በዘላለማዊ ቸርነቴ፣እራራልሻለሁ”ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።

9 “ይህ ለእኔ የኖኅ ውሃ ምድርን ዳግመኛ እንዳያጥለቀልቃት እንደማልሁበት፣እንደ ኖኅ ዘመን ነው፤አሁንም አንቺን ዳግም እንዳልቈጣ፣እንዳልገሥጽሽም ምያለሁ።

10 ተራሮች ቢናወጡ፣ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም”ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።