ኤርምያስ 13:16-22 NASV

16 ጨለማን ሳያመጣ፣በሚጨልሙትም ተራሮች ላይ፣እግሮቻችሁ ሳይሰናከሉ፣ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤እርሱ ወደ ጨለማ ይለውጠዋል፤ድቅድቅ ጨለማም ያደርገዋል።

17 ባትሰሙ ግን፣ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኮአልና፣ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።

18 ለንጉሡና ለእናቱ ለእቴጌዪቱ፣የክብር ዘውዳችሁ፣ከራሳችሁ ይወድቃልና፣ከዙፋናችሁ ውረዱ” በላቸው።

19 በኔጌቭ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ፤የሚከፍታቸውም አይኖርም፤ይሁዳ ሁሉ ተማርኮ ይሄዳል፤ሙሉ በሙሉም ይዘጋል።

20 ዐይኖቻችሁን ከፍታችሁ፣ከሰሜን የሚመጡትን እዩ።ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣የተመካሽባቸው በጎች የት አሉ?

21 ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽያስተማርሻቸው፣ባለ ሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ?እንደምትወልድ ሴት፣ምጥ አይዝሽምን?

22 “ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽራስሽን ብትጠይቂ፣ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።