ኤርምያስ 15:13-19 NASV

13 በመላ አገርህ፣ስላለው ኀጢአትህ ሁሉ፣ሀብትና ንብረትህን፣ያለ ዋጋ አሳልፌ ለምርኮ እሰጣለሁ።

14 ቍጣዬ በላያችሁ፣የሚነድ እሳት ትጭራለችና፣በማታውቀው አገር፣ለጠላቶችህ ባሪያ አደርግሃለሁ።”

15 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ፤እንግዲህ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ።ታጋሽ እንደ መሆንህ አታጥፋኝ፤ባንተ ምክንያት የሚደርስብኝን ነቀፋ አስብ።

16 ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በስምህ ተጠርቻለሁና፣ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።

17 ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋር አልተቀመጥሁም፤ከእነርሱም ጋር አልፈነጨሁም፤እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

18 ሕመሜ ለምን ጸናብኝ?ቍስሌስ ለምን በረታብኝ? ለምንስ የማይፈወስ ሆነ?እንደሚያታልል ወንዝ፣እንደሚያሳስት ምንጭ ትሆንብኛለህን?

19 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ብትመለስ፣ መልሼ አቆምሃለሁ፤ታገለግለኛለህም፤የከበረውን ከማይረባው ለይተህ ብትናገር፣አፍ ትሆነኛለህ፤እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ፣አንተ ወደ እነርሱ አትመለስም፤