ኤርምያስ 2:18-24 NASV

18 ከሺሖር ወንዝ ውሃ ለመጠጣት፣አሁንስ ለምን ወደ ግብፅ ወረድሽ?ከኤፍራጥስ ወንዝስ ውሃ ለመጠጣት፣ወደ አሦር መውረድ ለምን አስፈለገሽ?

19 ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤ክህደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤ እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ፣አስቢ፤ እስቲ አስተውዪ፤”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

20 “ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰበርሁ፤እስራትሽን በጣጠስሁ፤አንቺም፣ ‘አላገለግልህም’ አልሽ፤ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ሥር፣በያንዳንዱም ለምለም ዛፍ ሥር፣ለማመንዘር ተጋደምሽ።

21 እኔ፣ እንደ ምርጥ የወይን ተክል፣ጤናማና አስተማማኝ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ታዲያ ብልሹ የዱር ወይን ተክል ሆነሽ፣እንዴት ተለወጥሽብኝ?

22 በልዩ ቅጠል ብትታጠቢ፣ብዙ ሳሙና ብትጠቀሚም፣የበደልሽ ዕድፍ አሁንም በፊቴ ነው፤”ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

23 “ ‘አልረከስሁም፣በኣሊምን አልተከተልሁም’ እንዴት ትያለሽ?በሸለቆ ውስጥ ምን እንዳደረግሽእስቲ አስቢ፣ምንስ እንደ ፈጸምሽ ተገንዘቢ፤እንደምትፋንን ፈጣን ግመል ሆነሻል፤

24 በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤ከመጎምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል?ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም፤በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች።