ኤርምያስ 20:8-14 NASV

8 በተናገርሁ ቍጥር እጮኻለሁ፤“ሁከትና ጥፋት!” ብዬ ዐውጃለሁ፤ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል፣ቀኑን ሙሉ ስድብና ነቀፋ አስከተለብኝ።

9 ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የእርሱን ስም አላነሣም፤በስሙም አልናገርም” ብል፣ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም።

10 “በየቦታው ሽብር አለ፤አውግዙት፤ እናውግዘው፤”ብለው ብዙ ሲያንሾካሽኩ ሰማሁ፤መውደቄን በመጠባበቅ፣ባልንጀሮቼ የነበሩ ሁሉ፣“ይታለል ይሆናል፣ከዚያም እናሸንፈዋለን፤እንበቀለዋለንም” ይላሉ።

11 ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም።

12 ጻድቁን የምትፈትን ልብንና አእምሮን የምትመረምር፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ጒዳዬን ለአንተ አሳልፌ ሰጥቻለሁናስትበቀላቸው ለማየት አብቃኝ።

13 ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርቡ፤የችግረኛውን ነፍስ፣ከክፉዎች እጅ ታድጎአልና።

14 የተወለድሁባት ዕለት የተረገመች ትሁን፤እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን አትባረክ።