27 ልትመለሱባት ወደ ምትናፍቋት ምድር ከቶ አትመለሱም።”
28 ይህ ኢኮንያን የተባለ ሰው፣ የተናቀና የተሰበረ ገምቦ፣ማንም የማይፈልገው ዕቃ ነውን?እርሱና ልጆቹ ለምን ወደ ውጪ ተጣሉ?ወደማያውቁትስ ምድር ለምን ተወረወሩ?
29 ምድር ሆይ፤ አንቺ ምድር፣ አንቺ ምድር፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!
30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”