ኤርምያስ 49:26-32 NASV

26 በርግጥ ወንዶች ወጣቶቿ በየአደባባዩ ይረግፋሉ፤በዚያ ቀን ወታደሮቿ ሁሉ ይወድቃሉ፤”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤

27 “በደማስቆ ቅጥር ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤የወልደ አዴርንም ዐምባ ይበላል።”

28 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ወጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ ሐጾር መንግሥታት የተነገረ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ተነሡ፣ ቄዳርን ውጉ፤የምሥራቅንም ሕዝብ ደምስሱ።

29 ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው ይወሰዳሉ፤መጠለያቸውና ግመሎቻቸው ሳይቀሩ፣ከነዕቃዎቸው ይነጠቃሉ፤ሰዎች፣ ‘ሽብር በሽብር ላይ መጥቶባቸዋል፤’እያሉ ይጮኹባቸዋል።

30 በሐጾር የምትኖሩ ሆይ፣በጥድፊያ ሽሹ በጥልቅ ጒድጓድ ተሸሸጉ፤”ይላል እግዚአብሔር፤የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በእናንተ ላይ መክሮአልና፣ወረራም ዶልቶባችኋል።

31 “ተነሡ፣ ተዘልሎ የተቀመጠውን፣በራሱ ተማምኖ የሚኖረውን ሕዝብ ውጉ፤”ይላል እግዚአብሔር፤“መዝጊያና መቀርቀሪያ በሌለው፤ለብቻው በሚኖረው ሕዝብ ላይ ዝመቱ።

32 ግመሎቻቸው ይዘረፋሉ፤ከብቶቻቸውንም አንጋግተው ይነዱባቸዋል፤ጠጒሩን የሚቀነብበውን ወገንእበትናለሁ ከየአቅጣጫው መዓትይላል እግዚአብሔር፤