ኤርምያስ 50:31-37 NASV

31 “አንተ ትዕቢተኛ፤ እነሆ፣ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤“የምትቀጣበት ጊዜ፣ቀንህ ደርሶአልና።

32 ትዕቢተኛው ይሰናከላል፤ ይወድቃልም፤የሚያነሣውም የለም፤በዙሪያው ያሉትን ሁሉ የሚበላ እሳት፣በከተሞቹ ውስጥ አስነሣለሁ።”

33 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ፣በአንድነት ተጨቍነዋል፤የማረኳቸውም ሁሉ አጥብቀው ይዘዋቸዋል፤ይለቅቋቸውም ዘንድ እንቢ ብለዋል።

34 ነገር ግን ቤዛቸው ብርቱ ነው፤ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ለምድራቸው ዕረፍትን ለመስጠት፤ተግቶ ይሟገትላቸዋል፤በባቢሎን የሚኖሩትን ግን ዕረፍት ይነሣቸዋል።

35 “ሰይፍ በባቢሎናውያን ላይ መጣ!”ይላል እግዚአብሔር፤“በባቢሎን ነዋሪዎች ላይ፤በባለ ሥልጣኖቿና በጥበበኞቿም ላይ ተመዘዘ!

36 ሰይፍ በሐሰተኞች ነቢያቷ ላይ መጣ!እነርሱም ሞኞች ይሆናሉ፤ሰይፍ በጦረኞቿ ላይ ተመዘዘ፤እነርሱም ይሸበራሉ።

37 ሰይፍ በፈረሰኞቿና በሠረገሎቿ ላይ፣በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ሁሉ ላይ መጣ!እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ሰይፍ በሀብት ንብረቷ ላይ መጣ!ለዝርፊያም ይሆናሉ።