ኤርምያስ 51:5-11 NASV

5 ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ፊት፣በበደል የተሞላች ብትሆንም፣እስራኤልንና ይሁዳን አምላካቸው፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አልጣላቸውም።

6 “ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡፈጥናችሁም ሕይወታችሁን አትርፉ!በኀጢአቷ ምክንያት አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነው፤እርሱም የሥራዋን ይከፍላታል።

7 ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ምድርንም ሁሉ አሰከረች።ሕዝቦች ከወይን ጠጇ ጠጡ፤ስለዚህ አሁን አብደዋል።

8 ባቢሎን በድንገት ወድቃ ትሰበራለች፤ዋይ በሉላት!ምናልባት ልትፈወስ ስለምትችል፣ለቍስሏ የሚቀባ መድኀኒት ፈልጉላት።

9 “ ‘ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤እርሷ ግን ልትፈወስ አትችልም፤ፍርዷ እስከ ሰማይ ስለ ደረሰ፣እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ስላለ፣ትተናት ወደየአገራችን እንሂድ።’

10 “ ‘እግዚአብሔር ቅንነታችንን መሰከረ፤ኑ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ያደረገውን፣በጽዮን እንናገር።’

11 “ፍላጾችን ሳሉ፤ጋሻዎችን አዘጋጁ፤ የእግዚአብሔር ሐሳብ ባቢሎንን ለማጥፋት ስለ ሆነ፣የሜዶንን ነገሥታት አነሣሥቶአል፤ እግዚአብሔር ይበቀላል፤ስለ ቤተ መቅደሱ ይበቀላል።