26 የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ናቡዘረዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ የባቢሎን ንጉሥ ወደነበረበት ወደ ሪብላ አመጣቸው።
27 ንጉሡም በሐማት ምድር በነበረችው በሪብላ ፈጃቸው።ይሁዳም በዚህ ሁኔታ ከምድሯ በምርኮ ተወሰደች።
28 ናቡከደነፆር ማርኮ የወሰደው ሕዝብ ቍጥር እንደሚከተለው ነው፦በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፣ሦስት ሺህ ሃያ ሦስት አይሁድ፤
29 ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራስምንተኛው ዓመት፣ ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት ሰዎች ከኢየሩሳሌም፤
30 ናቡከደነፆር በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት፣ የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳንሰባት መቶ አርባ አምስት አይሁድ ማርኮ ወስዶአል፤በአጠቃላይ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች ነበሩ።
31 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ ዮርማሮዴክ በባቢሎን ነገሠ፤ በዚሁ ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን አሰበው፤ ከእስር ቤትም አወጣው፤
32 በመልካምም ቃል አናገረው፤ ከእርሱም ጋር በባቢሎን በምርኮ ከነበሩት ነገሥታት ይልቅ ከፍ ባለ የክብር ቦታ አስቀመጠው።