31 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ ዮርማሮዴክ በባቢሎን ነገሠ፤ በዚሁ ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን አሰበው፤ ከእስር ቤትም አወጣው፤
32 በመልካምም ቃል አናገረው፤ ከእርሱም ጋር በባቢሎን በምርኮ ከነበሩት ነገሥታት ይልቅ ከፍ ባለ የክብር ቦታ አስቀመጠው።
33 ዮአኪንም እስር ቤት ለብሶት የነበረውን ልብሱን አውልቆ ጣለ፤ በቀረውም የሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከንጉሡ ማእድ ይበላ ነበር።
34 የባቢሎንም ንጉሥ፣ ዮአኪን እስኪሞት ድረስ፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሳያቋርጥ በየዕለቱ ቀለቡን ይሰጠው ነበር።