ኤርምያስ 6:6-12 NASV

6 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ዛፎቹን ቍረጡ፤በኢየሩሳሌም ዙሪያ የዐፈር ድልድል ሥሩ።ይህቺ ከተማ ቅጣት ይገባታል፤ግፍን ተሞልታለችና።

7 የውሃ ጒድጓድ ውሃ እንደሚያመነጭ፣እርሷም እንዲሁ ክፋቷን ታፈልቃለች።ዐመፅና ጥፋት በውስጧ ይስተጋባል፤ሕመሟና ቍስሏ ዘወትር ይታየኛል።

8 ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተጠንቀቂ፤አለበለዚያ ከአንቺ ዘወር እላለሁ፤ማንም ሊኖርባት እስከማይችል ድረስ፣ምድርሽን ባዶ አደርጋለሁ።”

9 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው።ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።”

10 ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ?ማንስ ይሰማኛል?እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው አልተገረዙምና፣መስማት አይችሉም። በእግዚአብሔር ቃል ይሣለቃሉ፤ደስም አይሰኙበትም።

11 በእነርሱ ላይ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ፤በውስጤም ልይዘው አልቻልሁም።“መንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናት፣በተሰበሰቡ ወጣቶችም ላይ አፍስሰው፤ባልም ሚስትም፣ያረጁና የጃጁም አያመልጡም።

12 በምድሪቱ በሚኖሩት ላይ፣እጄን በምዘረጋበት ጊዜ፣ዕርሻቸውና ሚስቶቻቸው ሳይቀሩ፣ቤቶቻቸው ለሌሎች ይሆናሉ፤”ይላል እግዚአብሔር።