18 ገዡ ከንብረታቸው በማፈናቀል፤ የትኛውንም የሕዝቡን ርስት መውሰድ አይገባውም፤ ለወንድ ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ንብረት ነው፤ ይኸውም ከሕዝቤ ማንም ከርስቱ እንዳይነቀል ነው።’ ”
19 ከዚያም ያ ሰው በበሩ አጠገብ ባለው መግቢያ አድርጎ፣ ለሰሜን ትይዩ ወደሆኑት ወደ ካህናቱ የተቀደሱ ክፍሎች አመጣኝ፤ በምዕራቡም መዳረሻ ያለውን ቦታ አሳየኝ።
20 እርሱም፣ “ይህ ስፍራ ሕዝቡን ለመቀደስ መሥዋዕቱን ወደ ውጩ አደባባይ እንዳያወጡ፣ ካህናቱ የበደሉን መሥዋዕትና የኀጢአቱን መሥዋዕት የሚቀቅሉበት፣ የእህሉንም ቍርባን የሚጋግሩበት ቦታ ነው” አለኝ።
21 ከዚያም ወደ ውጩ አደባባይ አመጣኝ፤ በአራቱም ማእዘን ዙሪያ መራኝ፤ በእያንዳንዱም ማእዘን ሌላ አደባባይ አየሁ።
22 በውጩ አደባባይ ባለው በአራቱ ማእዘን የታጠሩ አደባባዮች አሉ፤ ርዝመታቸው አርባ ክንድ፣ ወርዳቸውም ሠላሳ ክንድ ነበር፤ በአራቱም ማእዘን ያሉት አደባባዮች እኩል ናቸው።
23 ከሥሩ ዙሪያውን ምድጃ የነበረበት፣ በአራቱም አደባባዮች ውስጥ ዙሪያ የድንጋይ ዕርከን ነበር።
24 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ፣ በቤተ መቅደሱ የሚያገለግሉቱ፣ የሕዝቡን መሥዋዕት የሚቀቅሉባቸው ስፍራዎች ናቸው።”