ሕዝቅኤል 16:30-36 NASV

30 “ ‘እንደ ዐይን አውጣ አመንዝራ ይህን ሁሉ መፈጸምሽ ምን ዐይነት ደካማ ልብ ቢኖርሽ ነው! ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

31 በየመንገዱ መጠምዘዣ ላይ ጒብታሽን ባበጀሽና በየአደባባዩም መስገጃ ኰረብታ በሠራሽ ጊዜ እንደ ማንኛውም ዝሙት አዳሪ አልነበርሽም፤ ምክንያቱም ዋጋ አላስከፈልሽም።

32 “ ‘አንቺ ከገዛ ባሏ ይልቅ ሌሎችን የምታስተናግድ አመንዝራ ነሽ!

33 ማንኛዋም አመንዝራ ሴት ዋጋ ይከፈላታል፤ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ስጦታ ታበረክቻለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋር ያመነዝሩ ዘንድ እጅ መንሻ ታቀርቢላቸዋለሽ።

34 ስለዚህ ያንቺ ግልሙትና ከሌሎቹ የተለየ ነው፤ ማመንዘር የሚሻ ማንም ሰው፣ አንቺን አሳዶ ማግባባት አያስፈልገውም። ዋጋ ትከፍያለሽ እንጂ አይከፈልሽም፤ አንቺ የሌሎች ፍጹም ተቃራኒ ነሽ።

35 “ ‘አንቺ አመንዝራ ሆይ፤ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!

36 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሀብትሽን ስላፈሰስሽ፣ ከወዳጆችሽ ጋር ያለ ገደብ ስላመነዘርሽና ዕርቃንሽን ስለ ገለጥሽ፣ ስለ አስጸያፊዎቹ ጣዖቶችሽ ሁሉና ለእነርሱም የልጆችሽን ደም ስላቀረብሽ፣