ሕዝቅኤል 7:4-10 NASV

4 በርኅራኄ ዐይን አልመለከትሽም፤ ምሕረትም አላደርግልሽም፤ ስለ አካሄድሽና በመካከልሽ ስላለው ጸያፍ ተግባር ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።”

5 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘መዓት! ተሰምቶ የማይታወቅ መዓት ይመጣል።

6 ፍጻሜ መጥቶአል! ፍጻሜ መጥቶአል! በአንቺ ላይ ተነሣሥቶአል፤ እነሆ፤ ደርሶአል!

7 እናንት በምድሪቱ የምትኖሩ ሆይ፤ የጥፋት ፍርድ መጥቶባችኋል፤ ጊዜው ደርሶአል፤ በተራሮች ላይ እልልታ ሳይሆን ሽብር የሚሰማበት ቀን ቀርቦአል።

8 እነሆ፤ መዓቴን በቅርብ ቀን አፈስብሻለሁ፤ በአንቺ ላይ ቍጣዬን እፈጽምብሻለሁ፤ እንደ አካሄድሽ እፈርድብሻለሁ፤ ስለ ጸያፍ ተግባርሽም ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ።

9 በርኅራኄ ዐይን አልመለከትሽም፤ ምሕረት አላደርግልሽም፤ ስለ አካሄድሽና በመካከልሽ ስላለው ጸያፍ ተግባር ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ፤ በዚያ ጊዜ፣ የምቀሥፍ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።

10 “ ‘እነሆ ቀኑ ይኸው ደረሰ! የጥፋት ፍርድ ተገልጦአል፤ በትሩ አቈጥቍጦአል፤ ትዕቢት አብቦአል።