15 እናንት፣ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል፤ከሲኦልም ጋር ስምምነት አድርገናል፤ውሸትን መጠጊያችን፣ሐሰትን መደበቂያችን አድርገናል፤ታላቅ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ሊነካን አይችልም” በማለት ታብያችኋል።
16 ስለዚህ ልዑል እግዚእብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ የተፈተነ ድንጋይ፣ የመሠረት ድንጋይ፣ለጽኑ መሠረት የሚሆን የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣በጽዮን አስቀምጣለሁ፤በእርሱም የሚያምን አያፍርም።
17 ፍትሕን የመለኪያ ገመድ፣ጽድቅንም ቱንቢ አደርጋለሁ፤ውሸት መጠጊያችሁን የበረዶ ዝናብ ይጠራርገዋልመደበቂያችሁንም ውሃ ያጥለቀልቀዋል።
18 ከሞት ጋር የገባችሁት ቃል ኪዳን ይሻራል፤ከሲኦልም ጋር ያደረጋችሁት ስምምነት ይፈርሳል፤ታላቁ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣እናንተም ትጠራረጋላችሁ።
19 በመጣ ቍጥር ይዞአችሁ ይሄዳል፤ማለዳ ማለዳ፣ በቀንና በሌሊትምይጠራርጋል።”ይህን ቃል ብታስተውሉ፣ሽብር በሽብር በሆነ ነበር።
20 እግር ዘርግቶ እንዳይተኛ ዐልጋው አጭር ነው፤ሰውነትንም ለመሸፋፈን ብርድ ልብሱ ጠባብ ነው።
21 እግዚአብሔር ሥራውን፣ አዎን ድንቅ ሥራውን ሊሠራ፣ተግባሩን፣ እንግዳ የሆነ ተግባሩን ሊያከናውን፣በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው ይነሣል፣በገባዖን ሸለቆ እንዳደረገው ይነሣሣል።