ኤርምያስ 18:12-18 NASV

12 እነርሱ ግን፣ ‘በከንቱ አትድከም፤ ባቀድነው እንገፋበታለን፤ እያንዳንዳችንም የክፉ ልባችንን እልኸኝነት እንከተላለን’ ይላሉ።”

13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እስቲ አሕዛብን፣‘እንዲህ ዐይነት ነገር በመካከላችሁ ተሰምቶ ያውቃል?’ ብላችሁ ጠይቁ።ድንግሊቱ እስራኤል፣እጅግ ክፉ ነገር አድርጋለች።

14 የሊባኖስ ተራራ ድንጋያማ ተረተር፣በረዶ ተለይቶት ያውቃልን?ከጋራው የሚወርደውስ ቀዝቃዛ ውሃ፤መፍሰሱን ያቋርጣልን?

15 ሕዝቤ ግን ረስቶኛል፤ለማይረቡ ነገሮች ዐጥኖአል፣በራሱ መንገድ፣በቀደሞው ጐዳና ተሰናክሎአል፤በሻካራው መሄጃ፣ባልቀናውም ጥርጊያ መንገድ ሄዶአል።

16 ምድራቸው ባድማ፣ለዘላለም መሣለቂያ ይሆናል፤በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤በመገረምም ራሱን ይነቀንቃል።

17 ከምሥራቅ እንደሚወጣ ነፋስ፣በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ፤በመጥፊያቸው ቀን፣ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”

18 እነርሱም፣ “ሕግ ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን፣ ቃልም ከነቢያት ስለማይታጣ ኑና በኤርምያስ ላይ እንማከር፤ ኑ፤ በአንደበታችን እናጥቃው፣ እርሱ የሚናገረውንም ሁሉ አንስማ” አሉ።