ኤርምያስ 38:10-16 NASV

10 ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን፣ “ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ይዘህ ሂድ፤ ነቢዩ ኤርምያስንም ሳይሞት ከጒድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው።

11 አቤሜሌክም ሰዎቹን ይዞ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ሥር ወዳለው ክፍል ሄደ፤ ያረጀ ጨርቅና ያለቀ ልብስ ከዚያ ወስዶ ወደ ኤርምያስ ወደ ጒድጓዱ ውስጥ በገመድ አወረደለት።

12 ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን፣ “ይህን ያረጀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ ገመዱ እንዳይከረክርህ በብብትህ ሥር አድርገው አለው፤ ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ፤

13 እነርሱም በገመዱ ጐትተው ከጒድጓዱ አወጡት። ኤርምያስም በዘበኞች አደባባይ ሰነበተ።

14 ንጉሡ ሴዴቅያስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ልኮ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስተኛው በር አስመጣውና፤ “አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው።

15 ኤርምያስም ሴዴቅያስን፣ “መልስ ብሰጥህ አትገድለኝምን? ምክር ብሰጥህ አትሰማኝም” አለው።

16 ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ “ለኤርምያስ፣ እስትንፋስ የሰጠ ሕያው እግዚአብሔርን! በእርግጥ አልገድልህም፤ ሕይወትህንም ለሚሿት አሳልፌ አልሰጥም” ብሎ በምስጢር ማለለት።