ኤርምያስ 8:13-19 NASV

13 “ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤ይላል እግዚአብሔር፤በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ።የሰጠኋቸው በሙሉ፣ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።’ ”

14 “ለምን እዚህ እንቀመጣለን?በአንድነት ተሰብሰቡ!ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ፤በዚያም እንጥፋ!በእርሱ ላይ ኀጢአትን ስላደረግን፣ እግዚአብሔር አምላካችን እንድንጠፋ አድርጎናል፤የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ ሰጥቶናል።

15 ሰላምን ተስፋ አደረግን፤መልካም ነገር ግን አልመጣም፤የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።

16 የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣ከዳን ይሰማል፤በድንጒላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች።ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣ሊውጡ መጡ።”

17 “እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰዳለሁ፤እነርሱም ይነድፉአችኋል፤”ይላል እግዚአብሔር።

18 በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ልቤ በውስጤ ዝላለች።

19 እንዲህ የሚለውን የሕዝቤን ጩኸት፣ከሩቅ ምድር ስማ፦ እግዚአብሔር በጽዮን የለምን?ንጉሥዋስ በዚያ አይኖርምን?”“በተቀረጹ ምስሎቻቸው፣እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ለምን አስቈጡኝ?”