ኤርምያስ 8:3-9 NASV

3 ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ሁሉ፣ ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፤ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’

4 “እንዲህ በላቸው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ሰዎች ቢውድቁ፣ እንደ ገና ከወደቁበት አይነሡምን?ሰው ተሳስቶ ወደ ኋላ ቢሄድ፣ ከስሕተቱ አይመለስምን?

5 ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል?ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች?ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።

6 እኔ በጥንቃቄ አደመጥኋቸው፤ትክክለኛ የሆነውን ግን አይናገሩም።ማንም ስለ ክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤“ምን አድርጌአለሁ?” ይላል።ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ፈረስ፣እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይሄዳል።

7 ሽመላ እንኳ በሰማይ፣የተወሰነ ጊዜዋን ታውቃለች፣ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳም፣የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ሕዝቤ ግን፣ የእግዚአብሔርን ሥርዐት አላወቀም።

8 “ ‘የጸሓፊዎቻችሁ ሐሰተኛ ብርዕ ሐሰትእያስተናገደ እንዴት፣ “ዐዋቂዎች ነን፣ የእግዚአብሔር ሕግ አለን” ትላላችሁ?

9 ጥበበኞች ያፍራሉ፤ይዋረዳሉ፤ በወጥመድም ይያዛሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ተቃውመው፣ምን ዐይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?