ኤርምያስ 14:17-22 NASV

17 “ይህን ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤“ ‘ድንግሊቱ ልጄ፣ ሕዝቤ፣በታላቅ ስብራት፣በብርቱ ቍስል ተመትታለችናዐይኖቼ ቀንና ሌሊት፣ ሳያቋርጡእንባ ያፈስሳሉ

18 ወደ ገጠር ብወጣ፣በሰይፍ የተገደሉትን አያለሁ፤ወደ ከተማ ብገባ፣ በራብ የወደቁትን አያለሁነቢዩም ካህኑም፣ወደማያውቁት አገር ሸሽተዋል።’ ”

19 ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን?ነፍስህስ ጽዮንን ተጸየፈቻትን?ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ፣ለምን ክፉኛ መታኸን?ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ሆኖም በጎ ነገር አላገኘንም፤የፈውስን ጊዜ ተጠባበቅን፤ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነ።

20 እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፋታችንን ዐውቀናልና፤የአባቶቻችንን በደል ተረድተናልና፤በእርግጥም በአንተ ላይ ኀጢአት ሠርተናል።

21 ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፤የክብርህንም ዙፋን አታዋርድ።ከእኛ ጋር የገባኸውን ኪዳን አስብ፤አታፍርሰውም።

22 ከአሕዛብ ከንቱ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለን?ሰማያትስ በራሳቸው ማካፋት ይችላሉን?አይ! አይችሉም፣ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ነህ፣ስለዚህም ተስፋችን በአንተ ላይ ነው።