1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን እንዲህ ርቀህ ቆምህ?በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ?
2 ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።
3 ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል።
4 ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤
5 መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው።በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል።