1 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ልመና አቀርባለሁ።
2 ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ።
3 መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፤ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል።
4 ወደ ቀኜ ተመልከት፤ እይም፤ስለ እኔ የሚገደው የለም፤ማምለጫም የለኝም፤ስለ ነፍሴም ደንታ ያለው የለም።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።
6 እጅግ ተስፋ ቈርጫለሁና፣ጩኸቴን ስማ፤ከዐቅም በላይ ሆነውብኛልና፣ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
7 ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።