መዝሙር
ምዕራፎች 39
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ታላቅ እግዚአብሔር - ታናሽ ሰው
ለመዘምራን አለቃ፣ ለኤዶታም፤ የዳዊት መዝሙር
1እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣መንገዴን እጠብቃለሁ፤ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ። 2እንደ ዲዳ ዝም አልሁ፤ለበጎ ነገር እንኳ አፌን ዘጋሁ፤ሆኖም ጭንቀቴ ባሰ። 3ልቤ በውስጤ ጋለ፤በማሰላስልበትም ጊዜ እሳቱ ነደደ፤ከዚያም በአንደበቴ እንዲህ ተናገርሁ፤ 4“እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ። 5እነሆ፤ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አስቀመጥህ፤ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፤በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ተን ነው። ሴላ 6ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤በከንቱም ይታወካል፤ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል። 7“ጌታ ሆይ፤ አሁንስ ወደ ማን ልመልከት?ተስፋዬ በአንተ ላይ ነው። 8ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤የሰነፎች መሣለቂያ አታድርገኝ። 9ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም። 10ክንድህን አንሣልኝ፤ከእጅህ ምት የተነሣ ደክሜአለሁና። 11ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤በእርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ 12“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ጩኸቴን አድምጥ፤ልቅሶዬንም ቸል አትበል፤በአንተ ፊት እኔ መጻተኛ ነኝና፤እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ። 13ላለመመለስ ከመሰናበቴ በፊት፣ዳግመኛ ደስ ይለኝ ዘንድ ዐይንህን ከላዬ አንሣ።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150