መዝሙር
ምዕራፎች 96
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔር፤ ንጉሥም ዳኛም
1 ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤ምድር ሁሉ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። 2 ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ። 3ክብሩን በሕዝቦች መካከል፣ድንቅ ሥራውንም በሰዎች ሁሉ ፊት ተናገሩ። 4 እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፤ ውዳሴም የሚገባው ነው፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ ሊፈራ ይገባዋል። 5የሕዝብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ። 6ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤ብርታትና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ አሉ። 7የሕዝቦች ወገኖች ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ። 8ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር ስጡ፤ቍርባንን ይዛችሁ ወደ አደባባዩ ግቡ። 9በተቀደሰ ውበት ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ። 10በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ነገሠ” በሉ፤ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥም፤እርሱ ለሕዝቦች በእኩልነት ይፈርዳል። 11ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤ 12መስኩና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ፤ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፤ 13እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤በዓለም ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150