1 ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።
2 ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤በዝማሬም እናወድሰው።
3 እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።
4 የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው።
5 እርሱ ፈጥሮአታልና፣ ባሕር የእርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።
6 ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤
7 እርሱ አምላካችን ነውና፤እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን።ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣
8 በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣በመሪባም እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።
9 ሥራዬን ቢያዩም፣አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።
10 ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤እኔም፣ “ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።
11 ስለዚህ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ብዬ፣በቍጣዬ ማልሁ።