መዝሙር
ምዕራፎች 8
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የፈጣሪ ግርማ በፍጥረቱ ላይ
ለመዘምራን አለቃ፣ በዋሽንት የሚዜም፤ የዳዊት መዝሙር
1 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ከፍ ከፍ ብሎአል። 2ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣ምስጋናን አዘጋጀህ፤ከጠላትህ የተነሣ፣ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ታሰኝ ዘንድ። 3የጣቶችህን ሥራ፣ሰማያትህን ስመለከት፣በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣ 4በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? 5ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤የክብርንና የሞገስን ዘውድ አቀዳጀኸው። 6በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛህለት፤ 7በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣የዱር አራዊትንም፣ 8የሰማይ ወፎችንና፣የባሕር ዓሦችን፣በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት። 9 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150