መዝሙር
ምዕራፎች 76
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ግርማው ለሚያሰፈራው አምላክ የቀረበ ቅኔ
ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች፤ የአሳፍ መዝሙር ማሕሌት
1እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፤ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው። 2ድንኳኑ በሳሌም፣ማደሪያውም በጽዮን ነው። 3በዚያም ተወርዋሪውን ፍላጻ፣ጋሻንና ሰይፍን፣ ጦርንም ሰበረ። ሴላ 4አንተ ብርሃን ተላብሰህ ደምቀሃል፤ግርማዊነትህም ከዘላለም ተራሮች ይልቃል። 5ልበ ሙሉ የሆኑት ተዘርፈዋል፤አንቀላፍተውም ተኝተዋል፤ከጦረኞቹም መካከል፣እጁን ማንቀሳቀስ የቻለ የለም። 6የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ከተግሣጽህ የተነሣ፣ፈረስና ፈረሰኛው ጭልጥ ብለው ተኝተዋል። 7መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል? 8አንተ ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፤ምድርም ፈርታ ጸጥ አለች፤ 9አምላክ ሆይ፤ ይህም የሆነው አንተ የምድር ጐስቋሎችን ለማዳን፣ለፍርድ በተነሣህ ጊዜ ነው። ሴላ 10ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ። 11ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተሳሉ፤ ስእለቱንም አግቡ፤በእርሱ ዙሪያ ያሉ ሁሉ፣አስፈሪ ለሆነው ለእርሱ እጅ መንሻ ያምጡ። 12እርሱ የገዦችን መንፈስ ይሰብራል፤በምድር ነገሥታትም ዘንድ የተፈራ ነው።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150