መዝሙር
ምዕራፎች 5
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የጧት ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ በዋሽንት የሚዘመር፣ የዳዊት መዝሙር
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ቃሌን አድምጥ፤መቃተቴንም ቸል አትበል። 2ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ድረስልኝ ብዬ ስጮህ ስማኝ። 3 እግዚአብሔር ሆይ፤ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤በማለዳ ልመናዬን በፊትህ አቀርባለሁ፤ፈቃድህንም በጥሞና እጠባበቃለሁ፤ 4አንተ በክፋት ደስ የምትሰኝ አምላክ አይደለህም፤ክፉም ከአንተ ጋር አያድርም። 5እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ። 6ሐሰት የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ደም የተጠሙትንና አታላዮችን፣ እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል። 7እኔ ግን በምሕረትህ ብዛትወደ ቤትህ እገባለሁ፤አንተንም በመፍራት፣ወደ ተቀደሰው መቅደስህ እሰግዳለሁ። 8 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጠላቶቼ የተነሣ፣በጽድቅህ ምራኝ፤መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ። 9በንግግራቸው ውስጥ እውነት የለም፤ልባቸው የጥፋት ጐሬ ነው፤ጒሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸውም ይሸነግላሉ። 10አምላክ ሆይ፤ የእጃቸውን ስጣቸው!ተንኰላቸው መውደቂያቸው ይሁን፤ከኀጢአታቸው ብዛት የተነሣ አስወግዳቸው፣በአንተ ላይ ዐምፀዋልና። 11አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፤ዘላለም በደስታ ይዘምሩ፤ስምህን የሚወዱ በአንተ ደስ እንዲላቸው፣ተከላካይ ሁንላቸው። 12 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቃንን ትባርካቸዋለህ፤በሞገስህም እንደ ጋሻ ትከልላቸዋለህ።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150