መዝሙር
ምዕራፎች 103
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔር ፍቅር ነው
የዳዊት መዝሙር
1ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪየውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ። 2ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤ 3ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣ 4ሕይወትሽን ከጥፋት ጒድጓድ የሚያድን፣ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣ 5ጐልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው። 6 እግዚአብሔር ለተጨቈኑ ሁሉ፣ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣቸዋል። 7መንገዱን ለሙሴ፣ሥራውንም ለእስራኤል ሕዝብ አሳወቀ። 8 እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፣ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩም የበዛ ነው። 9እርሱ ሁል ጊዜ በደልን አይከታተልም፤ለዘላለምም አይቈጣም። 10እንደ ኀጢአታችን አልመለሰልንም፤እንደ በደላችንም አልከፈለንም። 11ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት። 12ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ። 13አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል። 14እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ትቢያ መሆናችንንም ያስባል። 15ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤ 16ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤ምልክቱም በቦታው አይገኝም። 17 የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤ 18ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጉት ላይ ይሆናል። 19 እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል፤መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች። 20እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፤ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኀያላን፤ እግዚአብሔርን ባርኩ። 21እናንተ ፈቃዱን የምትፈጽሙ አገልጋዮቹ፤ሰራዊቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ። 22እናንተ በግዛቱ ሁሉ የምትኖሩ፣ፍጥረቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ፤ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150