መዝሙር
ምዕራፎች 21
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ምስጋና ስለ ንጉሡ
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥ በኀይልህ ደስ ይለዋል፤በምትሰጠውም ድል እጅግ ሐሤት ያደርጋል። 2የልቡን መሻት ሰጠኸው፤የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም። ሴላ 3መልካም በረከት ይዘህ በመንገዱ ላይ ጠብቀኸው፤የንጹሕ ወርቅ ዘውድም በራሱ ላይ ደፋህለት። 4ሕይወትን ለመነህ፤ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው። 5ባቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ክብርንና ሞገስን አጐናጸፍኸው። 6ዘላለማዊ በረከትን ሰጠኸው፤ከአንተ ዘንድ በሚገኝ ፍስሓም ደስ አሰኘኸው፤ 7ንጉሡ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፤ከልዑልም ጽኑ ፍቅር የተነሣ፣ከቆመበት አይናወጥም። 8እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታገኛቸዋለች፤ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ፈልጋ ትይዛለች። 9በምትገለጥበት ጊዜ፣እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በመዓቱ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል፤እሳቱም ሙጥጥ አድርጋ ትበላቸዋለች። 10ዘራቸውን ከምድር፣ዘር ማንዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ። 11ክፋት ቢያስቡብህ፣ተንኰል ቢወጥኑብህም አይሳካላቸውም፤ 12በመጡበት ትመልሳቸዋለህና፤ቀስትህንም በፊታቸው ላይ ታነጣጥራለህ። 13 እግዚአብሔር ሆይ፤ በብርታትህ ከፍ ከፍ በል፤ኀይልህን እናወድሳለን፤ እንዘምራለንም።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150