መዝሙር
ምዕራፎች 41
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የሕመምተኛና የብቸኛ ሰው ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር
1ለድኾች የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው፤እርሱንም እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል። 2 እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል፤በምድርም ላይ ይባርከዋል፤ለጠላቶቹም ምኞትም አሳልፎ አይሰጠውም። 3ታሞ ባለበት ዐልጋ ላይ እግዚአብሔር ይንከባከበዋል፤በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል። 4እኔም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረት አድርግልኝ፤አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት” አልሁ። 5ጠላቶቼ በክፋት በመናገር፣ “የሚሞተው መቼ ነው? ስሙስየሚደመሰሰው ምን ቀን ነው?” ይላሉ። 6ሊጠይቀኝ የሚመጣ ቢኖር፣በልቡ ስድብ እያጠራቀመ፣ ከዐንገት በላይ ይናገራል፤ወጥቶም ወሬ ይነዛል። 7ጠላቶቼ ሁሉ ግንባር ፈጥረው ይንሾካሾኩብኛል፤እንዲህ እያሉም፣የከፋ ነገር በላዬ ያውጠነጥናሉ፤ 8“ክፉ ደዌ ይዞታል፤ከእንግዲህም ከተኛበት አይነሣም።” 9እንጀራዬን ተካፍሎኝ የበላ፣የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ። 10 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ምሕረት አድርግልኝ፤የእጃቸውን እንድከፍላቸው አስነሣኝ። 11ጠላቴ በላዬ ድል አላገኘምና፣እንደ ወደድኸኝ በዚህ አወቅሁ። 12ስለ ጭንቀቴ ደግፈህ ይዘኸኛል፤በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ። 13የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ ይሁን፤አሜን፤ አሜን።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150