1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤ሐሳቤ ለዐጒል ትልቅነት አልተነሣሣም፤ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም።
2 ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሰኘኋት፤ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።
3 እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣ በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።