መዝሙር
ምዕራፎች 85
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ለሰላም የቀረበ ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች፤ መዝሙር
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ። 2የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ። ሴላ 3መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ። 4መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው። 5የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?ቊጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን? 6ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን? 7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤ማዳንህን ለግሰን። 8 እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ። 9ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ማዳኑ ለሚፈሩት በእርግጥ ቅርብ ነው። 10ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፤ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ። 11ታማኝነት ከምድር በቀለች፤ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች። 12 እግዚአብሔር በጎ ነገር ይለግሳል፤ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች። 13ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150