መዝሙር
ምዕራፎች 48
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የእግዚአብሔር ተራራ ጽዮን
ዝማሬ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር
1 እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባዋል። 2የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣በሰሜን በኩል በርቀት የሚታየው፣በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው። 3እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፤ብርቱ ምሽግ እንደሆናት አስመስክሮአል። 4እነሆ፤ ነገሥታት ተባብረው መጡ፤አንድ ላይ ሆነውም ገሠገሡ። 5አይተውም ተደነቁ፤ደንግጠውም ፈረጠጡ። 6ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣በዚያ ብርክ ያዛቸው። 7የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣አንተ አብረከረክሃቸው። 8እንደ ሰማን፣በሰራዊት አምላክ ከተማ፣በአምላካችን ከተማ፣እንዲሁ አየን፤እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ 9አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ምሕረትህን እናስባለን። 10አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት። 11ስለ ፍርድህ፣የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው። 12በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤የጥበቃ ግንበኞቿንም ቍጠሩ፤ 13ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ። 14ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150