መዝሙር
ምዕራፎች 4
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
የሠርክ ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዜም የዳዊት መዝሙር
1የጽድቄ አምላክ ሆይ፤በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፤ከጭንቀቴ አሳርፈኝ፤ማረኝ፤ ጸሎቴንም ስማ። 2ሰዎች ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ዝቅ ታደርጋላችሁ?እስከ መቼስ ድረስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ? ሐሰትንስ ትሻላችሁ? ሴላ 3 እግዚአብሔር ጻድቁን ለራሱ እንደ ለየ ዕወቁ፤ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል። 4ስትቈጡ ኀጢአት አትሥሩ፤በዐልጋችሁም ላይ ሳላችሁ፣ልባችሁን መርምሩ፤ ጸጥም በሉ። ሴላ 5የጽድቅን መሥዋዕት አቅርቡ፤ በእግዚአብሔርም ታመኑ። 6ብዙዎች፣ “አንዳች በጎ ነገር ማን ያሳየናል? ይላሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የፊትህ ብርሃን በላያችን ይብራ። 7ስንዴና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ባመረቱ ጊዜ ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ፣አንተ ልቤን በታላቅ ሐሤት ሞልተኸዋል። 8በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150