1 ስለ ምሕረትና ስለ ፍትሕ እዘምራለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአንተ በምስጋና እቀኛለሁ።
2 እንከን የማይገኝባትን መንገድ አጥብቄ እይዛለሁ፤አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው?በቤቴ ውስጥ፣በንጹሕ ልብ እመላለሳለሁ።
3 በዐይኔ ፊት፣ክፉ ነገር አላኖርም።የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ከእኔም ጋር አይጣበቅም።
4 ጠማማ ልብ ከእኔ ይርቃል፤ለክፋትም ዕውቅና አልሰጥም።
5 ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣አጠፋዋለሁ፤ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣እርሱን አልታገሠውም።
6 ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ፣ዐይኖቼ በምድሪቱ ታማኞች ላይ ናቸው፤በንጽሕና መንገድ የሚሄድ፣እርሱ ያገለግለኛል።
7 አታላይ የሆነ ማንም ሰው፣በቤቴ ውስጥ አይኖርም፤ሐሰትን የሚናገር፣በፊቴ ቀና ብሎ አይቆምም።
8 በምድሪቱ ላይ ያሉትን ክፉዎች ሁሉ፣በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ፣ ከእግዚአብሔር ከተማ እደመስሳቸዋለሁ።