መዝሙር
ምዕራፎች 6
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
በጭንቅ ጊዜ የቀረበ ጸሎት
ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች የሚዘመር፤ የዳዊት መዝሙር በሸሚኒት
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህአትገሥጸኝ፤በመዓትህም አትቅጣኝ። 2 እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐቅመ ቢስ ነኝና ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐጥንቶቼ ተናግተዋልና ፈውሰኝ። 3ነፍሴ እጅግ ታውካለች፤እስከ መቼ፤ አንተ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ድረስ ይሆናል? 4 እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስና ሕይወቴን ታደጋት፤ስለ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ፤ 5በሞት የሚያስታውስህ የለምና፤በሲኦልስ ማን ያመሰግንሃል? 6ከመቃተቴ የተነሣ ዝያለሁ፤ሌሊቱን ሁሉ በልቅሶ ዐልጋዬን አርሳለሁ፤መኝታዬንም በእንባዬ አሾቃለሁ። 7ዐይኖቼ በሐዘን ብዛት ደክመዋል፤ከጠላቶቼም ሁሉ የተነሣ ማየት ተስኖአቸዋል። 8እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቶአልና። 9 እግዚአብሔር ልመናዬን አድምጦአል፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል። 10ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ እጅግም ይደነግጣሉ፤በመጡበት ይመለሳሉ፤ ድንገትም ይዋረዳሉ።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150