መዝሙር
ምዕራፎች 92
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ጻድቅ ሰው ሲደሰት
በሰንበት ቀን የሚዘመር መዝሙር፤ ማሕሌት
1 እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፤ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤ 2ምሕረትህን በማለዳ፣ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤ 3ዐሥር አውታር ባለው በገና፣በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው። 4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ። 5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው!ሐሳብህስ ምን ያህል ጥልቅ ነው! 6ደነዝ ሰው ይህን አያውቅም፤ነኁላላም አያስተውለውም። 7ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣ለዘላለሙ ይጠፋሉ፤ 8 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም ልዑል ነህ። 9ጠላቶችህ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፤ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይበተናሉ። 10የእኔን ቀንድ ግን እንደ አውራሪስ ቀንድ ከፍ ከፍ አደረግኸው፤በለጋ ዘይትም አረሰረስኸኝ። 11ዐይኖቼ የባላንጦቼን ውድቀት አዩ፤ጆሮዎቼም የክፉ ጠላቶቼን ድቀት ሰሙ። 12ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ። 13 በእግዚአብሔር ቤት ተተክለዋል፤በአምላካችንም አደባባይ ይንሰራፋሉ። 14ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ፤እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ። 15“እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤እርሱ ዐለቴ ነው፤ በእርሱ ዘንድ እንከን የለም” ይላሉ።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150