መዝሙር
ምዕራፎች 111
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ለመለኮቱ ባሕርያት የቀረበ ጸሎት
1ሃሌ ሉያ።በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ። 2 የእግዚአሔር ሥራ ታላቅ ናት፤ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል። 3ሥራው ባለ ክብርና ባለ ግርማ ነው፤ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። 4ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤ እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው። 5ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል። 6ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣የአሠራሩን ብርታት አሳይቶአል። 7የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው፤ሥርዐቱም ሁሉ የታመነ ነው፤ 8ከዘላለም እስከ ለዘላለም የጸና ነው፤በእውነትና በቅንነትም የተሠራ ነው። 9ለሕዝቡ መዳንን ሰደደ፤ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው። 10 እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።ምዕራፎች
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
15
16
17
18
19
20
21
22
23
24
25
26
27
28
29
30
31
32
33
34
35
36
37
38
39
40
41
42
43
44
45
46
47
48
49
50
51
52
53
54
55
56
57
58
59
60
61
62
63
64
65
66
67
68
69
70
71
72
73
74
75
76
77
78
79
80
81
82
83
84
85
86
87
88
89
90
91
92
93
94
95
96
97
98
99
100
101
102
103
104
105
106
107
108
109
110
111
112
113
114
115
116
117
118
119
120
121
122
123
124
125
126
127
128
129
130
131
132
133
134
135
136
137
138
139
140
141
142
143
144
145
146
147
148
149
150